በሱዳን ጉዳይ የፀጥታው ምክር ቤት ዝግ ስብሰባ ዛሬ ያካሂዳል

ጥቅምት 16/2014 (ዋልታ) የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በሱዳን በተፈፀመው መፈንቅለ መንግሥስት ጉዳይ አስቸኳይ ዝግ ስብሰባ ዛሬ ያካሂዳል፡፡
አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ አየርላንድ፣ ኖርዌይ እና ኢስቶኒያ ናቸው የፀጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲደረግ የጠየቁት፡፡
የምክር ቤቱ ልዑክ በማሊ እና በኒጀር ያደረገውን ጉብኝት አጠናቆ ዛሬ ከሰአት በኋላ ወደ ኒውዮርክ እንደሚመለስ እና ስብሰባው 10:00 እንደሚካሄድ አሶሼትሰ ፕረስ ዲፕሎማቶችን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ እና ሌሎች የአገሪቱ ሲቪል ባለሥልጣናት መታሰራቸው ይታወቃል፡፡
በዚህም የተለያዩ አገራትና ኅብረቶች በሱዳን የተፈፀመውን መፈንቅለ መንግሥት በማውገዝ መግለጫ እያወጡ ይገኛሉ፡፡