በሴቶች የ10 ኪ.ሜ ሩጫ ኢትዮጵያ በአትሌት ፅጌ ገ/ሰላማ የብር ሜዳሊያ አገኘች

የካቲት 11/2015 (ዋልታ) በአውስትራሊያ ባተርስት በተካሄደው የሴቶች የ10 ኪ.ሜ ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያ በአትሌት ፅጌ ገ/ሰላማ የብር ሜዳሊያ አገኘች።

በውድድሩ አትሌት ለተሰንበት ግደይ የመጨረሻው ሪቫን ልትበጥስ ጥቂት እርምጃዎች እንደቀሯት ቁርጭምጪሚቷ አካባቢ በደረሰባት የእግር መታጠፍ በመውደቋ ውድድሩን መጨረስ እንዳልቻለች የኢትዮጵያ አቲሌትክስ መረጃ ያመላክታል።

በውጤቱ መሠረትም በውድድሩ የተሳተፉት ፅጌ ገ/ሰላማ 2ኛ፣ ፎቲን ተስፋይ 5ኛ፣ ሃዊ ፈይሳ 6ኛ፣ ጌጤ አለማዬሁ 12ኛ እንዲሁም ውዴ ከፋለ 15ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡