በተቀናጀ የግብርና ሥርዓት ተጠቃሚ መሆናቸውን የካፋ ዞን ነዋሪዎች ገለፁ

መጋቢት 24/ 2014 (ዋልታ) በተቀናጀ የግብርና ሥርዓት የበለጠ ተጠቃሚ መሆናቸውን የካፋ ዞን ነዋሪዎች ገለፁ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ጡላ ቀበሌና ቦንጋ ከተማ የማር ምርት የቦንጋ የዶሮ እርባታ፣ የዓሳ አምራችና እንስሳት እርባታ ማዕከላትን ጎብኝተዋል።
በክልሉ የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማትን ለማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ምክክር ተጀምሯል።
በመስክ ምልከታው ወቅት የአካባው አርሶ አደሮች በወተት አቅርቦት በጣዝማ ማር ምርት በዶሮ እርባታ የተሻለ ወጤት ማግኘታቸውን ገልፀው አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ላይ የሚታዩ መልካም ተሞክሮዎችን በማጠናከር በመስክ ምልከታው የተነሱ ጉድለቶችን ለማሻሻል ክልሉ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ማሰረሻ በላቸው በበኩላቸው የተቀናጀ የግብርና ልማት ዘዴን በመከተል አርሶ አደሩ ከጓሮው የተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ማግኘት ከተቻለ ምርታማና ጤነኛ ዜጋን ማፍራት ይቻላል ብለዋል።
አክሊሉ ሲራጅ (ከቦንጋ)