“የተካደው የሰሜን ዕዝ ” መፅሐፍ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት በብሔራዊ ቴአትር እየተመረቀ ነው

መጋቢት 24/2014 (ዋልታ) በደራሲ ሃምሳ አለቃ ጋሻዬ ጤናው የተጻፈው “የተካደው የሰሜን ዕዝ ” መፅሐፍ በብሔራዊ ቴአትር እየተመረቀ ይገኛል፡፡
በደራሲ ሃምሳ አለቃ ጋሻዬ ጤናው ተፅፎ ለንባብ በበቃው በዚህ መፅሐፍ ምረቃ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተገኙ ሲሆን የሰሜን ዕዝ የደረሰበትን በደል እና ክህደት ለታሪክ ፅፎ ያኖረውን ደራሲ አመስግነዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሸባሪው ሕወሓት በወንድሞቹ ላይ ጦር ስብቆ ያደረሰው በደል እንዲህ በአገር ወዳድ ልጆቿ ተመክቶ እኩይ ሴራው ሲፈርስ እና የነበረ ዕውነታውን ሲያኖር ድርብ ድል ነው ብለዋል።
በሰሜን እዝ ጥቃት ወቅት በስፍራው የነበረው 50 አለቃ ጋሻዬ ጤናው የመፅሐፉ ማስታወሻነት ለአገራቸው አንድነት እና ሉአላዊነት ለተሰው ጀግኖች ነው ብሏል።
በቁምነገር አሕመድ