በትግራይ ባሉ እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተወሰነ

ጥቅምት 9/2014 (ዋልታ) በአሸባሪው ሕወሓት ቡድን በተፈጠረው ችግር ምክንያት በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎችና በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

በየኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲ በጊዜያዊነት ለመመደብ የመመዝገቢያ ገፅ ተከፍቶ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ እና ምደባ እንደሚካሄድም ተገልጿል፡፡

በዚህም በዩኒቨርስቲዎቹ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃቸውን በማዘጋጀት ከዛሬ ጀምሮ መመዝገብ እንደሚችሉ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።