በትግራይ ክልል ባሉ ክለቦች ሲጫወቱ ለነበሩ ተጫዋቾች የተፈቀደው ልዩ የዝውውር ጊዜ ተራዘመ 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በትግራይ ክልል ባሉ ክለቦች ሲጫወቱ ለነበሩ ተጫዋቾች የፈቀደው ልዩ የዝውውር ጊዜ እስከ ጥር 3 ቀን 2013 ተራዝሟል።

ዝውውሩ በክልሉ በነበረው ሰላም የማስከበር ሥራ ምክንያት በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ የነበሩ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ከታኅሣሥ 26-30 ቀን 2013 ዓ.ም ለአምስት የሥራ ቀናት የተፈቀደ ነበር።

የማራዘሚያ ቀናት የተሰጠው ታኅሣሥ 29 የገና በዓል በመሆኑ የተነሣ ምክንያት እንደሆነም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።