በትግራይ ክልል ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ከዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው

ሰኔ 25/2013(ዋልታ) – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እንዲሁም በአምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በትግራይ ክልል ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ከዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ጋር ውይይት እያካሄዱ ነው።

በውይይቱ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የበርካታ ሀገራት አምባሳደሮች እና የዲፕሎማቲክ አባላት ተሳትፈውበታል።

የኢትዮጵያ መንግስት ለተሻለ ሠላም ብሎም የትግራይ አርሶ አደሮች የግብርና ስራቸውን በነፃነት እንዲከውኑ በማሠብ የተናጠል የተኩስ አቁም ስምምነት ማድረጉን አቶ ደመቀ መኮንን በውይይቱ መክፈቻ ላይ ተናግረዋል።

ሽብርተኛው የህወሀት ጁንታ በትግራይ ክልል የሚገኙ መሰረተ ልማቶችን በማፈራረስ መንግስት ከፍተኛ ወጭ እንዲያወጣና ፈተና እንዲገጥመው አድርጓል ሲሉም ተናግረዋል።

ከዚህም በተጨማሪ የመንግስትን እርምጃ በአልተገባ መንገድ በመተርጎም ወደ አልተገባ አቅጣጫ የሚወስዱ አካላትም ከድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ አቶ ደመቀ አሳስበዋል።
(በድልአብ ለማ)