በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ክለሳ ተደረገ

ከጥር 30 ቀን 2013 ጀምሮ እስከ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ የነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ክለሳ መደረጉን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር  አስታወቀ።

በክለሳ ዋጋው መሠረት ፡-

ቤንዚን 25 ብር ከ82 ሳንቲም

ኢታኖል ድብልቅ ቤንዚን 25 ብር ከ32 ሳንቲም

ነጭ ናፍጣ 23 ብር ከ04 ሳንቲም

ኬሮሲን 23 ብር ከ04 ሳንቲም

ቀላል ጥቁር ናፍጣ 20 ብር ከ27 ሳንቲም

ከባድ ጥቁር ናፍጣ 19 ብር ከ77 ሳንቲም

የአውሮፕላን ነዳጅ 35 ከ12 ሳንቲም መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ክለሳው ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በመላው አገሪቱ በሚገኙ አካባቢዎች እንደየርቀታቸው መጠን ከዛሬ  ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጿል።