በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የድጋፍ ሰልፎች እየተደረጉ ነው

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መንግስት የድጋፍ ሰልፎች እየተደረጉ ነው፡፡

የሀረሪ ክልል ነዋሪዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መንግስት አመራር የመጣውን ሀገራዊ ለውጥ በመደገፍ  ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡

በድጋፍ ሰልፉም “አሸናፊ ሐሳብን እናራምዳለን፣  ፅንፈኝነተን አምርረን እንታገለዋለን!፤ ብልፅግና የሁሉም ችግሮች መፍቻ ቁልፍ ነዉ!፤ ከብልፅግና ጋር ስኬታማ እንደምንሆን አንጠራጠርም!” የሚሉ መፈክሮችን በመያዝ ድጋፋቸውን እየገለፁ ይገኛሉ፡፡

በድጋፍ ሰልፉም በክልሉ ከገጠርና ከተማው የተወጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

በተመሳሳይ ሀገራዊ ለውጡን በመደገፍ በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ መሆኑን ከክልሉ እና ከዞኑ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡