“በነፃ ያስተማረችንን ሀገር ውለታ ለመመለስ የተማርንባቸውን ትምህርት ቤቶች መደገፍ ያስፈልጋል” – አርቲስት ዘለቀ ገሰሰ

አርቲስት ዘለቀ ገሰሰ

ሐምሌ 23/2015(ዋልታ) በነፃ ያስተማረችንን ሀገር ውለታ በማሰብ የተማርንባቸውን ትምህርት ቤቶች መደገፍና ማስዋብ ያስፈልጋል ሲል አርቲስት ዘለቀ ገሰሰ ተናገረ።

አርቲስቱ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል በትምህርት ቤቶች ደረጃ ማሻሻያ ንቅናቄው ላይ ተሳታፊ እንዲሆንም ጥሪውን አቅርቧል።

አርቲስቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለው “ትምህርት ለትውልድ” ሀገራዊ ንቅናቄ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ጠቅሶ በዚህ አጋጣሚም በነፃ ያስተማረችንን ሀገር ውለታ በማሰብ የተማርንባቸውን ትምህርት ቤቶች በመደገፍ ደረጃቸውን ማሻሻል ያስፈልጋል ብሏል።

በኢትዮጵያ ሕዝብ ድጋፍ ሀገር በነፃ ነው ያስተማረችን ያለው አርቲስቱ በተለያዩ የዓለም ክፍል የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም የተማሩባቸውን ትምህርት ቤቶች ክፍተት ለመሙላት ድጋፍ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ተናግሯል።