በአለም በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 100 ሚሊየን አለፈ

 

በአለም ዙሪያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 100 ሚሊየን ማለፉ ተሰምቷል፡፡

እስካሁን በአለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሚሊየን 286 ሺህ 772 ሆኗል፡፡

በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም 2 ሚሊየን 149 ሺህ 496 ደርሷል፡፡

በቫይረሱ የተያዙ ዜጎቿ ቁጥር ከ25 ሚሊየን በላይ የሆነባት አሜሪካን ጨምሮ ህንድ፣ ብራዚል፣ ሩሲያ እና ብሪታኒያ ከፍተኛ ተጽዕኖ ውስጥ የወደቁ አገራት መሆናቸው ይጠቀሳል፡፡

በአንጻሩ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከ72 ሚሊየን 313 ሺህ 625 ናቸው ፡፡
(ምንጭ፡- ዎርልድ ኦ ሜትር)