ለወጣቶች የተዘጋጀ ሀገር አቀፍ የብሔራዊ በጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልገሎት ሥልጠና ተጀመረ

ለወጣቶች የተዘጋጀ ሀገር አቀፍ የብሔራዊ በጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልገሎት ሥልጠና በአሶሳ እና ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲዎች ዛሬ ተጀመረ።

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተጀመረው ሥልጠና ከኦሮሚያ፣ አማራ፣ ሲዳማ ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝጉ እና ደቡብ ክልሎች የተወጣጡ የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ 350 በጎ ፈቃደኞች እየተሳተፉ ነው።

በተመሳሳይ በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በተጀመረው ሥልጠና ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተወጣጡ 487 ወጣቶች እየተሳተፉ ነው።

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳን ዶክተር ኡጁሉ ኡኮክ በሥልጠና መከፈቻ ሥነ-ሥርዓት ወቅት እንዳሉት በሀገሪቱ አሁን ለተገኘው ለውጥ የወጣቱ ሚና ከፍተኛ ነው።

ይህንን ታሳቢ በማድረግ ይህንን ሃይል በሀገራዊ የውጥና የብልጽግና ጉዞ ውስጥ ተሳትፎውን ለማጠናከር ሥልጠናው አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።

ሥልጠናውን ያዘጋጁት በሠላም ሚነስቴርና ዩኒቨርሲቲዎች የጋር ትብብር ሲሆን በሌሎችም ዩኒቨርሲቲዎች ተመሳሳይ ሥልጠናዎች መኖራቸውንም ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የሠላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል በቪዲዮ ኮንፍረንስ ለሠልጣኞቹ መልዕክት እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል።