በአምቦ የቀድሞ 04 ቀበሌ ምርጫ ጣቢያ መራጮች በንቃት ድምጽ እየሰጡ ነው

ሰኔ 14/2013 (ዋልታ) – ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚወዳደሩት የብልፅግና ፓርቲ እጩ አቶ ሳህሉ ድሪብሳ በአምቦ የቀድሞ 04 ቀበሌ ምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምፅ ሰጥተዋል።
በአምቦ ምርጫ ክልል 1 በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች መራጮች ድምፅ እየሰጡ ይገኛል።
በአምቦ ምርጫ ክልል አንድ 94 የምርጫ ጣቢያዎች ሲኖሩ፣ 69,696 ዜጎች የመራጭነት ካርድ ወስደዋል።
(በደረሰ አማረ)