በአሸባሪው ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ2 ሚሊየን ዶላር በላይ ተሰበሰበ

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ

ኅዳር 18/2014 (ዋልታ) ዳያስፖራው በአገር ቤት በአሸባሪው ሕወሓት ወረራ ለተጎዱ ወገኖች በ ‘eyezonethiopia.com’ መተግበሪያ አማካኝነት ያሰባሰበው ገንዘብ ከ2 ሚሊየን ዶላር በላይ መድረሱን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

ኤጀንሲው ከቻፓ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ ጋር በመተባበር ባለማውና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባመቻቸው ዓለም አቀፍ የክፍያ መተግበሪያ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር በላይ ማሰባሰብ ተችሏል።

ይህም ዳያስፖራው ምቹ ሁኔታ እስከተፈጠረለት ድረስ ሀገሩን ለመርዳት ያለውን ዝግጁነትና ዕምቅ አቅሙን ያሳያል ነው የተባለው።

በድጋፉ ላይ ለተሳተፉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምስጋና ያቀረበው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዳያስፖራው ድጋፉን አጠናክሮ በመቀጠል የአገር አለኝታነቱን ዳግም እንዲያረጋግጥ ጠይቋል።