በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ለመከላከያ ሰራዊት የስንቅ ዝግጅት እየተከናወነ ይገኛል

ሐምሌ 17/2013 (ዋልታ) – በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኙ አራት ወረዳዎች በጋራ በመሆን ለመከላከያ ሰራዊት ስንቅ በማዘጋጀት ላይ ይገኛሉ።

የአሸባሪውን ህወሀት ቡድን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ በማጥፋት አገራዊ አንድነት እና ህዝባዊ ሰላምን ለማረጋገጥ መስዋዕትነት የሚከፍለውን የአገር መከላከያ ሰራዊት መደገፍ የዜግነት ግዴታችን ነው ሲሉ ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያውያን ለጠላት የማይበገሩ በአገራዊ አንድነታቸው የማይደራደሩ ናቸው ያሉት በስንቅ ዝግጅት ላይ ያገኘናየው ነዋሪዎቹ  መከላከያ ሰራዊቱ ሰብአዊነት መለያው የሆነ  ከህዝብ ወጥቶ  ለህዝብ የቆመ የምንግዜም ኩራታችን ነው ብለዋል።

(በቁምነገር አህመድ)