“በአዋሽ አርባ ዛሬ የተመለከትነው የተቀናጀ የውጊያ ልምምድ ኢትዮጵያ ጦርነትን የሚያስቀር ኃይል መገንባቷን ነው” – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ጥር 20/2015 (ዋልታ) በአዋሽ አርባ ዛሬ የተመለከትነው የተቀናጀ የውጊያ ልምምድ ኢትዮጵያ ጦርነትን የሚያስቀር ኃይል መገንባቷን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምልከታቸውን ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት በውጊያ ልምምዱ አየር ኃይል ፣ ከባድ መሳሪያ ፣ልዩ ኃይል እና እግረኛ ተቀናጅቶ ውጊያን በአጭር የሚያስቀርባቸውን መንገዶች ተመልክተናል ብለዋል።

“በየቀኑ አይናችንን ከምንፈልገው ህልም እና ተግባራችን እንድናነሳ የሚሹ ኃይሎች ስላሉ የጦር መኮንኖች ዋና ተግባር የሚሆነው ጦርነትን የሚያስቀር ኃይል መገንባት ነው ” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፡፡