በአየር ጸባይ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ የሚደረጉ በረራዎች አቅራቢያ በሚገኙ አውሮፕላን ማረፊያዎች እንዲያርፉ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ሐምሌ 19/2013 (ዋልታ) – በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ በተፈጠረው መጥፎ የአየር ጸባይ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ የሚደረጉ በረራዎች አቅራቢያ በሚገኙ አውሮፕላን ማረፊያዎች እንዲያርፉ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ ጉዳዩን አስመልከቶ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባስተላለፈው መልዕክት፣ በተፈጠረው መጥፎ የአየር ጸባይ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ የሚደረጉ በረራዎች አቅራቢያ በሚገኙ አውሮፕላን ማረፊያዎች እንዲያርፉ እየተደረገ ነው ብሏል፡፡

የተፈጠረው አየር ጸባይ ችግር ሲስተካከል ለደንበኞቹ እንደሚያሳውቅም ነው የገለጸው፡፡

ከአየር መንገዱ አቅም በላይ ለተፈጠረው ችግርም ደንበኞችን ይቅርታ ጠይቋል፡፡