በእስራኤል እና ሞሮኮ መካከል የቀጥታ በረራ ተጀመረ


ሐምሌ 19/2013 (ዋልታ) –
በእስራኤል እና ሞሮኮ መካከል ተቋርጦ የነበረው የንግድ አውሮፕላኖች የቀጥታ በረራ እንደገና ተጀመረ።
በሁለቱ አገራት መካከል በረራው እንዲጀመር ያስቻለው ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ ላይ ሁለቱ አገራት ግንኙነታቸውን ለማሻሻል በመስማማታቸው ነው። ይህ ስምምነት የአረብ አገራት ከእስራኤል ጋር ያላቸውን ግንኙነት መደበኛ ለማድረግ ሲያካሂዷቸው የነበሩ ተከታታይ ስምምነቶች አካል አንዱ ነው።
ኤል አይ እና አሰረኤይር የተባሉ ሁለት የእስራኤል አየር መንገዶች ከቴል አቪቭ የጎብኚዎች መዳረሻ ወደሆነችው የሞሮኮዋ ማራካሽ ከተማ ተጓዦችን ማመላለስ የጀመሩ ሲሆን፣ አየር መንገዶቹ መደበኛ የጉዞ እቅዶችንም ይፋ አድርገዋል።
የሁለቱን አገራት ግንኙነት ለማሻሻል አሜሪካ ትልቅ ሚና የተጫወተች ሲሆን፣ ይህም የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሞሮኮ በምዕራብ ሳህራ ላይ ያላትን የሉአላዊነት ጥያቄ እውቅና ከሰጡ በኋላ መጠናከን ቢቢሲ ዘግቧል።