በአፍሪካ አመራር የልህቀት አካዳሚና በቻይናው ናሽናል አካዳሚ ገቨርናንስ መካከል በትብብር ለመስራት የሚስችል ሰነድ ተፈረመ

ጥቅምት 28/2016 (አዲስ ዋልታ) የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከቻይናው ናሽናል አካዳሚ ገቨርነንስ አካዳሚ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ሰነደ ተፈራረመ።

ብቃት ያላቸው አመራሮችን ለማፍራት የሚሠራው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በስራው የረጅም ዓመት ልምድ ካለው የቻይናው አካዳሚ  ገቨርናንስ ጋር መስራቱ አመራሮች ብቁ ሆነው እንዲወጡ ልምድ ለማግኘት እንደሚረዳ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርእሰ አካዳሚ የሆኑት ዛድግ አብረሀ ተናግረዋል።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከብዙ ሀገሮች ጋር ትስስር እየፈጠረ መሆኑንና  በአመራር ብቃት ትልቅ ደረጃ ካለው የቻይና ናሽናል አካዳሚ ገቨርናንስ ጋር  ተቀራርቦ ለመማማር  ይህ ስምምነት አስፈላጊ መሆኑ ተጠቁሟል።

በቤዛዊት አበበ