በኢትዮጵያና በሲዊዘርላንድ መንግስታት መካከል ተደራራቢ ግብርን የሚያስቀር ስምምነት ተፈረመ


ሐምሌ 22/2013 (ዋልታ) –
በኢትዮጵያና በሲዊዘርላንድ መንግስታት መካከል ተደራራቢ ግብርን ለማስወግድ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ፡፡
የስምምነቱ አላማ የሲዊዘርላንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ሀብታቸውን በልማት ስራ ላይ እንዲያውሉ ለማበረታታትና የኢትዮጵያም ባለሀብቶች በሲዊዘርላድ ገበያ ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማስቻል መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ አስታውቀዋል፡፡
ተደራራቢ ግብር ለውጭ ኢንቨስትመንት ማነቆ በመሆኑ ከሲዊዘርላንድ መንግስት ጋር ሶስት ዙር ድርድር በማድረግ የተደራራቢ ግብርን ለማስገድ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
የተደራራቢ ግብር ማስወገድ ስምምነት የውጭ ኢንቨስትመንትን ለማበረታት የሚያግዝ ከመሆኑም በላይ የግብር ማጭበርበርን በመከላከል ገቢ ለሀገር ልማትና እንድገት እንዲውል የላቀ አስተዋጽኦ እንዳለውም ተገልጿል፡፡
ስምምነቱ በገንዘብ ሚኒስትሩር አቶ አህመድ ሺዴ እና በኢትዮጵያ የሲዊዘርላንድ አምባሳደር ታማራ ሞና መፈረሙን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡