የአረንጓዴ አሻራ፣ የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ማደስና የፅዳት ዘመቻ መርሃ ግብር በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ ነው

ሐምሌ 22/2013 (ዋልታ) – የ2013 የአረንጓዴ አሻራ፣ የክረምት በጎ ፈቃድ የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ማደስና የፅዳት ዘመቻ መርሃ ግብር በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የምስራቅ ኢትዮጰያዋ የንግድና ኢንዱስትሪ ከተማዋ ድሬደዋ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች የ2013 የአረንጓዴ አሻራና የክረምት በጎ ፈቃድ የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ማደስና የፅዳት ዘመቻ መርሃ ግብር ተመራጭ ከተማ ሆናለች።

የከተማው መስተዳደር አመራሮች፣ የሐይማኖት አባቶች በጎአድራጊ ተቋማትና የወጣት አደረጃጀቶች በዚህ ተምሳሌታዊ በጎ ተግባር እየተሳተፉ እንደሚገኙ ከቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።