በኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ምክር ቤት ተመሰረተ

በኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ምክር ቤት ተመሰረተ። የምክር ቤቱ የምስረታ ጉባኤ  ላይ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶችን የወከሉ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

ዘርፉ የበቃና በነጻነት የተደራጀ፣ በሃሳብ ልዕልና የሚያምን፣ አገራዊ ክብርን የሚያስጠብቅ፣ በራሱ የሚተማመን አምራች ዜጋን በማፍራት ረገድም  ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም ጠቁመዋል።

ድርጅቶቹ ለትርፍ ያልተቋቋሙ እንደመሆናቸው መጠን ለማህበረሰቡ የሚጠቅም ስራ መስራታቸውን የሚያረጋግጡበት እራሱን የቻለ ስርአት ማበጀት እንደሚገባቸውም ነው የተናገሩት።

በቅርቡ የተሻሻለው የሲቪል ማኅበራት አዋጅም ምክር ቤቱ  እንዲመሰረት ጉልህ ሚና መጫወቱንም ገልጸዋል።

የምክር ቤቱ መመስረት ዘርፉ በጠንካራ ተቋም የመወከል እንደሚያስችልም ጠቁመዋል።

ድርጅቶቹ አሰራራቸውን ግልጽ እና ተጠያቂነት ያለበት እንዲሆን በማድረግ ምክር ቤቱ የተለያዩ ተግባራትን ያከናውናል ነው ያሉት።

ምክር ቤቱ የሚያወጣቸውን የስነ-ምግባር ደንቦች በሁሉም የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ላይ ተግባራዊ የሚያደርግ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ምክር ቤቱ ማህበራቱ በስነ-ምግባር የታነጹ፣ የማህበረሰብ ጥቅም የሚሰሩ፣ ከሙስናና ከብልሹ አሰራር የፀዱ፣ ህብረተሰቡን በነጻነት የሚያገለግሉና እና ተቀባይነት ያላቸው እንዲሆኑም ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።