በኤርትራ የጥምቀት በዓል ተከበረ

በኤርትራ የጥምቀት በዓል

ጥር 11/2014 (ዋልታ) የኢየሱስ ክርስቶስን በዮርዳኖስ ወንዝ በመጥምቁ ዮኀንስ እጅ መጠመቅን መነሻ አድርጎ በየዓመቱ ጥር 11 የሚከበረው የጥምቀት በዓል በኤርትራ ተከበረ።

የአገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በዓሉ የኮቪድ-19 መከላከያ መመሪያዎችን በጠበቀ መልኩ በዋና ከተማዋ አስመራ በድምቀት መከበሩን በቲውተር ገጻቸው ጽፈዋል።

በዓሉ በኤርትራ ቴሌቪዥን የ2 ሰዓት የቀጥታ ሽፋን እንደነበረውም ጠቅሰዋል።