በእንሰት ተክል ዙሪያ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ ጉባኤ እየተካሄደ ነው


ጳጉሜን 1/2015 (አዲስ ዋልታ) በእንሰት ዙሪያ የተዘጋጀ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ ጉባኤ በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ ነው።

የእንሰት ተክል በደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በስፋት የሚለማና ከ20 ሚሊየን በላይ የሚሆን ህዝብ ለምግብነት የሚጠቀመው ቢሆንም እንደሀገር ያልተጠቀምንበት ሀገር በቀል የምግብ ምንጭ መሆኑ ተገልጿል።

በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ አስተናጋጅነት በሚካሄደው በዚህ ሲምፖዚየም የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የግብርና ቢሮ ኃላፊ ኦስማን ሱሩር፣ የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዳምጠው ደርዛ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ምሁራን ተገኝተዋል።

እንሰት ሀገራዊ የምግብ ደህንነትን ከማረጋገጥ በተጨማሪ ለዓለም ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኝ ከመሆኑ አንፃር ተገቢውን ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተመላክቷል።

የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ከግብርና ሚኒስቴር እና ከተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ አጋሮች ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ይህ ጉባኤ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን በእንሰት ዙሪያ የተካሄዱ ምርምሮች ይቀርቡበታል ተብሎም ይጠበቃል።

በሔኖክ ኃይሉ