በኦሮሚያ በቱሪዝም ዘርፍ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዷል

ኅዳር 2/2014 (ዋልታ) በቀጣይ 5 ዓመት በቱሪዝም ዘርፉ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር እቅድ መያዙን የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ማኅበረሰቡን በሚጠቅምና በአገር ምጣኔሃብት ላይ ለውጥ በሚያመጣ መልኩ እንደሚሰራም ተጠቁሟል።

ኮሚሽኑ በክልሉ የሚገኙ እምቅ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማልማት በዚህም ሰፊ የአገር ውስጥ የውጭ ጉብኝዎችን ቁጥር ለመሳብ አልሞ እየሰራ ነው፡፡

በሳራ ስየም