በጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢንቨስት የሚያደርጉ ቻይናዊያን ባለሃብቶችን ጅማ ገቡ

ነሐሴ 3/2015 (አዲስ ዋልታ) የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሚ እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢንቨስት የሚያደርጉ ቻይናዊያን ባለሀብቶችን ይዘው ጅማ ከተማ መግባታቸው ተገለጸ።
በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዝዩአን ጨምሮ በጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢንቨስት ለማድረግ የሚፈልጉ በርካታ የቻይና ባለሀብቶች ወደ ጅማ ከተማ ተጉዘው በኢንዱስትሪ ፓርኩ ጉብኝት እያደረጉ መሆናቸውም ተመላክቷል።
ከጉብኝት መርኃ ግብሩ ባሻገር ባለሀብቶቹ ለኢንቨስትመንት ስምምነት የፊርማ ሥነ ስርዓት ያከናውናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።