በጤናው ዘርፍ የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ሁሉም አካላት በኃላፊነት መስራት እንዳለባቸው ሚኒስትሯ አመላከቱ

ዶክተር ሊያ ታደሰ

ሐምሌ 22/2014 (ዋልታ) በጤናው ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት እና በ2015 በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ሁሉም አካላት በኃላፊነት መስራት እንዳለባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አመላከቱ።

በሚኒስቴሩ የ2015 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ዶክተር ሊያ ታደሰ የቀጣይ በጀት ዓመት ሁሉም እቅዶች ሪፎርሙን ተከትሎ መታቀዳቸውን ተናግረዋል።

የመንግሥት ክትትልና ድጋፍ በጤናው ዘርፍ መጨመሩ የተጠቆመ ሲሆን በአዲሱ በጀት ዓመት መንግሥት ለጤናው ዘርፍ የበጀተው በጀት ከአምናው ጋር ሲነፃፀር መጨመሩ ተጠቁሟል፡፡

ለጋሽ ድርጅቶች የሚያደርጉት ድጋፍ መቀነሱን ያስታወሱት ሚኒስትሯ የ2015 በጀት ዓመት በጀትን ችግር ፈቺ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ማዋል እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በአርባምንጭ ከተማ የ2015 የበጀት ዓመት የሚኒስቴሩ እቅድ ላይ ውይይት እየተካሄደ መሆኑን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW