በ1500 ሜትር ወንዶች ማጣሪያ ሁለት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለግማሽ ፍጻሜ አለፉ

ሐምሌ 26/2013 (ዋልታ) – በ1500 ሜትር ወንዶች ማጣሪያ ታደሰ ለሚ እና ሳሙኤል አባተ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አልፈዋል፡፡

ከምድብ ሁለት አትሌት ሳሙኤል አባተ በ3፡41.63 5ኛ ደረጃ ይዞ ሲያጠናቅቅ ፤ከምድብ ሶስት አትሌት ታደሰ ለሚ በ3፡36.26 2ኛ ደረጃ በመየዝ የግማሽ ፍፃሜው ውድድር መቀላቀላቸውን ከኢትዮጵያ አትሌትክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

በምድብ አንድ የተወዳደረውና በ3፡37.78 9ኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው አትሌት ሳሙኤል ተፈራ ለግማሽ ፍፃሜው ማለፍ አልቻለም።