ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ ከአውስትራሊያ ጊዜያዊ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

ሐምሌ 26/2013 (ዋልታ) – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ ከአውስትራሊያ ጊዜያዊ አምባሳደር ጄኒ ዳን ረን ጋር  ተወያዩ።

በውይይታቸውም ቀጣይ በከተማ ደረጃ በሚተገበሩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ በሰፊው መክረው መግባባት ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህም በከተሞች የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ በአቅም ግንባታ እንዲሁም በንግድና ኢንቨስትመንት ስራዎች ዙሪያ በጋራ ለመስራት መስማማተቸውንም ከአዲስ አበባ ከተማ ፐሬስ ሴክሬተሪ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የአውስትራሊያ ጊዜያዊ አምባሳደር ጄኒ ዳን ረን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በአውስትራሊያ ባለሀብቶች ድጋፍ ሊገነባ የታሰበውን “የልጆች ተስፋ” የወላጅ አልባና ችግረኛ ህጻናት ማሳደጊያና መንከባከቢያ ማዕከልን ግንባታ እውን ለማድረግ እስካሁን ከ200 ሚሊየን ብር በላይ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።