በ2.3 ቢሊየን ብር ወጪየተገነቡት የመማሪያ ክፍልና የመመገቢያ አዳራሽ ተጠናቀው ተመረቁ

 

የመማሪያ ክፍልና የመመገቢያ አዳራሾች

የካቲት 11 ቀን 2013 (ዋልታ) – በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጪ የመማሪያ ክፍልና የመመገቢያ አዳራሽ ማስፋፊያ ግንባታዎች ተጠናቀው ተመረቁ።

ከ1 ሺህ 700 በላይ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች እና ከ230 በላይ የመመገቢያ አዳራሾች በዛሬው ዕለት ተመርቀው ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

ለግንባታው 2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ የተማሪዎችን ተጋላጭነት ለመቀነስ እንዲሁም ‹‹የክፍል-ተማሪ›› ጥምርታን ለማሻሻል በማሰብ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የመማሪያ ክፍል ማስፋፊያ እንዲደረግ ልዩ ውሳኔ ማሳለፉን የአስተዳደሩ ፕሬስ ስክሬተሪያት አስታውሷል።

የማስፋፊያ ግንባታዎቹ በአስሩም ክፍለ ከተሞች በሚገኙና በተመረጡ 150 ትምህርት ቤቶች ነው የተካሄደው፡፡

በምርቃ ሥነ-ሥርዐቱ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር ዓባይ፣ የትምህርት ሚኒስትሩር ዶክተር ኢንጂነር ር ጌታሁን መኩሪያ እና የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው ዕንግዶች ተገኝተዋል።