በ2022 ተቃራኒ ሐሳብ ካላቸው አገራት ጋር ጠንካራ የዲፕሎማሲ ሥራ እንደሚሰራ ተገለፀ

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

ታኅሣሥ 28/2014 (ዋልታ) የጎርጎሮሲያኑ 2022 ዋና አጀንዳ የኢትዮጵያን ሉኣላዊነት ማስጠበቅ እና ተቃራኒ አጀንዳ ካላቸው አገራት ጋር ጠንካራ የዲፕሎማሲ ሥራ መስራት እንደሆነ መንግሥት አስታወቀ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ሳምንታዊ መግለጫ የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሰጥተዋል፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ያለፈው 2021 ኢትዮጵያ ላይ ከውስጥም ከውጭም ከፍተኛ ጫና የተደረገበት ዓመት እንደነበር ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ በጠንካራ ሕዝቦቿ፣ በውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጥረት እና በተለያዩ አጋር አገራት ትብብር ጫናውን በመቀልበስ ኢትዮጵያ ማሸነፏን ተናግረዋል።

በዋናነት በኢትዮጵያ ላይ ሲደረግ የነበረው ጫና የታላቁ ኅዳሴ ግድብን እና በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተወሰደውን ሕግ የማስከበር እርምጃን እንደ ጭንብል በመጠቀም መሆኑንም አመልክተዋል።

ሜሮን መስፍን