ኅዳር 12/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በወቅታዊ ጉዳዮች ከመምህራን ጋር ወይይት እያደረገ ይገኛል፡፡
ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ከህዝብ እና ከግል ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ከ2ሺሕ 200 በላይ መምህራን ናቸው በወቅታዊ ጉዳይ እየተወያዩ የሚገኙት፡፡
በመርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላት በወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታ ላይ ለመምህራን የመነሻ ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡
ከመድረኩ መምህራን ለሀገራዊ ጥሪ ምላሽ እንዲሠጡም ይጠበቃል ነው የተባለው።
በሰለሞን በየነ