ባለስልጣኑ በ5 ወራት ከ741.9 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

ታኅሣሥ 5/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በበጀት ዓመቱ ያለፉት አምስት ወራት 741 ሚሊየን 987 ሺሕ ብር በላይ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡
ባለስለጣኑ በአምስቱ ወራት 776 ሚሊየን 350 ሺሕ 677 ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ 741 ሚሊየን 987 ሺሕ ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 96 በመቶ ማሳካቱን ገልጿል፡፡
ገቢው በውሃ አገልግሎት ዘርፍ ከሚሠጡ የውሃ ሽያጭ፣ የቆጣሪ ግብር፣ ከውሃ መስመር ቅጥያ እንዲሁም በፍሳሽ አገልግሎት ዘርፍ ከፍሳሽ ማንሳት አገልግሎት፣ ከአዲስ ደንበኞች የፍሳሽ መስመር ቅጥያ አገልግሎት እና ከሌሎች ተጨማሪ አገልግሎቶች መሰብሰቡም ተጠቁሟል፡፡
ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ ከ1 ቢሊየን 705 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሰበሰብ ዕቅድ ይዞ እየሠራ እንደሆነም ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡