በ2013 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከበይነ-መንግሥታዊ ተቋማት እና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት 53.44 ቢሊዮን ብር የተገኘ ሲሆን፣ ከመንግሥታት ትብብር 23.89 ቢሊዮን ብር በጥቅሉ 77.33 ቢሊዮን ብር መገኘቱን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ከውጭ ብድር 14.79 ቢሊዮን ብር ከበይነ-መንግሥታዊ ተቋማት እና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት የተገኘ ሲሆን፣ 2.9 ቢሊየን ብር ከመንግሥታት ትብብር ምንጭ ተገኝቷል ተብሏል።
ከእርዳታ 38.65 ቢሊዮን ብር ከበይነ-መንግሥታዊ ተቋማት እና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት የተገኘ ሲሆን፣ 20.9 ቢሊየን ብር ከመንግሥታት ትብብር የተገኘ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያ ከሁለት ዋና፣ ዋና ምንጮች የውጭ ብድር እና እርዳታ ለልማት ፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ እንደምታገኝ የተገለጸ ሲሆን፣ አንደኛው ከበይነ-መንግሥታዊ ተቋማት እና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ሲሆን፣ ሁለተኛው ከመንግሥታት ትብብር ምንጭ መሆኑን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።