ባንኩ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የ281 ሚሊዮን ዶላር የብድር መተማመኛ አጸደቀ

ታኅሣሥ 14/2015 (ዋልታ) የአሜሪካው ኤክስፖርት ኢምፖርት ባንክ (EXIM Bank ) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የ281 ሚሊዮን ዶላር የብድር መተማመኛ አጸደቀ፡፡

ባንኩ በይፋዊ ድረ ገፁ ላይ እንዳስታወቀው ውሳኔው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ አውሮፕላኖችን ለመግዛት የሚረዳ ነው፡፡

የብድር መተማመኛው መፈቀዱ የሁለቱ ሀገራትን የጋራ ብልፅግና እና ትብብር ማሳያ ነውም ተብሏል፡፡