ብሔራዊ ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ ሲደርስ አቀባበል ተደረገለት

ነሐሴ 23/2015(አዲስ ዋልታ) በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሄራዊ ቡድን አዲስ አበባ ገብቷል ።

በሀንጋሪ የተሳተፈው ልኡክ ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል ።

በአቀባበል ስነስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ብርቱካን አያኖና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ ጨምሮ ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ለልኡክ ቡድኑ የአበባ ጉንጉን አበርክተዋል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን በውድድሩ 2የወርቅ 4የብር እና 3 የነሀስ በጥቅሉ 9ሜዳሊያ በማግኘት ከዓለም 6ኛ ከአፍሪካ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቁ የሚታወስ ነው፡፡

በሙባረክ ፋንታሁን