ብሪታንያ አስትራዜኒካ የተሰኘውን የኮሮናቫይረስ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቀደች

ብሪታንያ በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች የበለጸገውን አስትራዜኒካ የተሰኘውን የኮሮናቫይረስ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቀደች፡፡

በሀገሪቷ ባሉ የመድሐኒት ተቆጣጣሪዎች ክትባቱ ደህንነቱ የተጠበቀ ፍቱንና ፈዋሽ መሆኑ መረጋገጡ ነው የተሰማው፡፡

አስትራዜኒካ በብሪታንያ ፍቃድ ሲያገኝ ከፋይዘርና ከባዮንቴክ በመቀጠል ሁለተኛው ነው ተብሏል፡፡

እንዲሁም ከሌሎቹ ክትባቶች አንጻር ሲታይ በመደበኛ ማቀዝቀዣዎች ውስጥ ማስቀመጥ እንደሚቻል የተጠቀሰ ሲሆን ይህም ለአጠቃቀም እና ለአያያዝ ምቹ ያደርገዋል ነው ያሉት፡፡

ብሪታንያም 50 ሚሊየን ዜጎቿን መከተብ የሚያስችል 100 ሚሊየን መጠን የያዘ ክትባት ማዘዟን ገልጻለች፡፡

የዛሬ ዓመት ጥር አካባቢ ማበልጸግ የተጀመረው ይህ ክትባት ሚያዝያ ላይ በበጎፍቃደኞች ከተሞከረ በኋላ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ክሊኒካል ሙከራ መካሄዱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡