የወንጀለኛ መቅጫና ማስረጃ ረቂቅ ሕጎች ከሰብዓዊ መብት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ተከታትሎ ለማስፈጸም ያስችላሉ – ዶክተር ዳንኤል በቀለ

 

የወንጀለኛ መቅጫና ማስረጃ ረቂቅ ሕጎች ከሰብዓዊ መብት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ተከታትሎ ለማስፈጸም የሚያስችሉ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በወንጀለኛ መቅጫና ማስረጃ ረቂቅ ህጎች ላይ የሚመክር መድረክ እያካሔደ ነው።

ኮሚሽነሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የኢፌዴሪ ረቂቅ የወንጀለኛ ሕግ ሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ መዘጋጀቱ ትልቅ እርምጃና ለዓመታት የታዩ ችግሮችን መቅረፍ የሚያስችል ነው።

ረቂቅ ሕጉ ከክስ ምስረታ እስከ ምርመራ ከምርመራ እስከ ፍርድ አሰጣጥ ያሉ ሒደቶችንና የዳኝነት ሕጎችን የሚፈትሽ መሆኑንም ገልጸዋል።

“ሕጉ ከሰብዓዊ መብት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ተከታትሎ ለማስፈጸም የሚያስችል ነው” በማለት አስታውቀዋል።

ለሚቀጥሉት ረጅም ዓመታት ገዢ ሆኖ የሚቀጥል ረቂቅ ሕግ ስለሆነ በጥልቀት መወያየትና መስራት ያስፈልጋል ሲሉም አመልክተዋል።

ሕጉ ከሌሎች ሕጎች ጋር ተናባቢና ተጣጥሞ የሚሄድ መሆኑም መፈተሽ እንዳለበት ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

በመድረኩ ላይ ረቂቅ ሕጎቹ የያዟቸው ዝርዝር ጉዳዮች እየተዳሰሱ ይገኛሉ።

(ምንጭ፡-ኢዜአ)