ከፔሌ በፊት እግር ኳስ ስፖርት ብቻ ነበር፤ ፔሌ ግን እግር ኳስን ጥበብ አደረገ – ብራዚላዊው ኮኮብ ኔይማር ጁኒየር

ኔይማር ጁኒየር

ታኅሣሥ 21/2015 (ዋልታ) ከፔሌ በፊት እግር ኳስ ስፖርት ብቻ ነበር፤ ፔሌ ግን እግር ኳስን ጥበብ አድርጎ ሁሉንም ነገር የቀየረ ንጉስ ነው ሲል ብራዚላዊው ኮኮብ ኔይማር ጁኒየር ገለጸ።

ብራዚላዊው የእግር ኳስ ፈርጥ ፔሌ ህልፈትን ተከትሎ የዓለማችን ታዋቂ የስፖርት ሰዎች እና ፖለቲከኞች ለተጨዋቹ ያላቸውን ክብር በማህበራዊ ትስስር ገፅ እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

ለፔሌ ክብራቸውን ከገለፁ መካከል አንዱ ብራዚላዊው የእግር ኳስ ኮኮብ ኔይማር ጁኒየር ሲሆን ፔሌ ሁሉን ነገር የቀየረ ንጉስ ነው ሲል ከፔሌ በፊት እግር ኳስ ስፖርት ብቻ ነበር ፔሌ ግን እግር ኳስን ጥበብ በማድረግ ይበልጥ ሳቢ እና አዝናኝ እንዲሆን ያደረገ የምንጊዜም ጀግና ነው ብሏል፡፡

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በበኩላቸው ፔሌ የስፖርትን አቅም በመረዳት ህዝቦችን አንድ ያደረገ ጀግና ነው ሲሉ ለቤተሰቦቹ እና ወዳጆቹ መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡

የፈንሳዩ ኮኮብ ኪሊያን ምባፔ እሱ የምንጊዜም የእግር ኳስ ኮከብ ነው ሲል የእሱ ጀግንነት እና ታሪክ ሁሌም ሲታወስ ይኖራል ሲል ገልጾታል፡፡