የተባበሩት መንግሥታት ለ7 ሀገራት የረሀብ አደጋን ለመቋቋም 100 ሚሊዮን ዶላር መደበ

ሚያዚያ 7/2014 (ዋልታ) የተባበሩት መንግሥታት በአፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ አገራት ሊያጋጥም የሚችል የረሀብ አደጋን ለመቋቋም 100 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን አስታወቀ።
ድጋፉ ለኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ ኬንያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ናይጄሪያ እንዲሁም ለየመን የሚከፋፈል እንደሆነ ተገልጿል።
ኢትዮጵያ ከ100 ሚሊዮን ዶላሩ ውስጥ 12 ሚሊዮን ዶላር እንደምታገኝ ተገልጿል፡፡
ድጋፉን ያደረገው በዩክሬንና ሩስያ መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት በአፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ በሚሊየን በሚቆጠሩ ዜጎች ላይ የከፋ የረሀብ አደጋ ሊደቅን ይችላል የሚል ስጋት ስላለው መሆኑን አስታውቋል፡፡
በሀገራቱ የምግብ ዋስትና እንዳይረጋገጥ ድርቅ፣ የትጥቅ ትግል እና የምጣኔሃብት አለመረጋጋት እንደዋነኛ ምክንያት ቢጠቀሱም የዩክሬን ቀውስ ችግሩን እንዳባባሰው የቻይና ዜና አገልግሎት ኤጀንሲ ሺንዋ አስነብቧል፡፡