ግንቦት 3/2014 (ዋልታ) የዓለም ጤና ድርጅት በአገሪቱ የኮቪድ-19 ቁጥጥር ፖሊሲ ዙሪያ የሰጠው አስተያየት ኃላፊነት የጎደለው ነው ሲሉ የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዛሆ ሊጃን ገለጹ።
ቃል አቀባዩ ቻይና በማኅበረሰብ ደረጃ የኮቪድ 19 ቫይረስ ስርጭትን ወደ ዜሮ ማውረድ ላይ ትኩረት አድርጋ እየሰራች መሆኗን አስታውቀዋል።
የሚኒስትሩ ቃል አቀባይ አክለውም የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተሩ የቻይና የኮቪድ ፖሊሲ ተሞክሮ በፍትሐዊነት እና ከአድልኦ በጸዳ መልኩ እንደሚመለከቱት ተስፋ አደርጋለው ማለታቸውን ኢቢሲ ሮይተርስን ጠቅሶ ዘግቧል።
ቃል አቀባዩ ይህንን የገለጹት የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ቻይና ኮቪድ ላይ የምትከተለው ፖሊሲ ቀጣይነት የለውም ሲሉ መተቸታቸውን ተከትሎ ነው የተባለው።
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW