ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አህመድ በአንድነት ለጋራ ዓላማ መቆም ተግዳሮቶችን ለመሻገር አቅም እንደሚሆን ገለጹ

ግንቦት 3/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአንድነት ለጋራ ዓላማ መቆም ተግዳሮቶችን ለመሻገር እንዲሁም ለሀገር ዘላቂ ብልጽግናን ለመገንባት አቅም እንደሚሆን ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአማራ ክልል መስተዳድር በሕግ ማስከበር ዘመቻው ወቅት አስተዋጽዖ ላበረከቱ አካላት ባዘጋጀው የምስጋና እና የዕውቅና መርሐ ግብር ላይ ለፌደራል የጸጥታ አካላትና ተቋማት ሽልማት ማበርከታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።