ኅብረተሰቡ ሐሰተኛ መረጃ በመሠራጨት ላይ መሆኑን ዐውቆ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ

ሚያዝያ 26/2013 (ዋልታ) – ኅብረተሰቡ ሐሰተኛ መረጃ በመሠራጨት ላይ መሆኑን ዐውቆ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አሳሰበ፡፡

“የወንጀለኞች ቡድን ከቀድሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የግል የኢሜይል አድራሻ የተላከ በማስመሰል  መረጃ በመጠየቅ እና ሐሰተኛ ምላሽ በመስጠት ላይ መሆናቸውን ዐውቀናል” ሲል ጽ/ቤቱ አስታውቋል።

“በመሆኑም ሁሉም ሰው ሐሰተኛ መረጃ በመሠራጨት ላይ መሆኑን ዐውቆ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ እና እንደዚህ ያሉ አጠራጣሪና ጥፋት የሚያስከትሉ እንቅስቃሴዎችን ለሕግ አስከባሪ አካላት እንዲያሳውቅ እናሳስባለን” ብሏል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባሰፈረው መልዕክት።