ነገ የምንፈልጋትን ሀገር ለመገንባት በዛሬው ትውልድ ላይ መሥራት ይኖርብናል – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

የካቲት 14/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነገ የምንፈልጋትን ሀገር ለመገንባት በዛሬው ትውልድ ላይ መሥራት ይኖርብናል ሲሉ አሳሰቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በልደታ ክፍለ ከተማ ሳር ቤት አካባቢ እንደ አዲስ የተገነባውን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ስራ አስጀምረዋል።

የስፖርት ማዘውተሪያው ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት እና በሁሉም የበቃ ትውልድ ለመፍጠር ያለመ ነው።