አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከቻይና አምባሳደር ጋር ተወያዩ

ግንቦት 23/2013 (ዋልታ) – በሱዳን የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከቻይና ህዝባዊት ሪፐብሊክ አምባሳደር ማ ዚንሚንጋር በወቅታዊ አገራዊና ቀጠናው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

በዚህ ወቅት አምባሳደር ይበልጣል በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ፣ ስድስተኛውን ሀገራዊ ምርጫ በተመለከተ እየተደረገ ስላለው ዝግጅት፣ ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና የኢትዮጵያ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ የኢትዮጵያን አቋም አስረድተዋል፡፡

የቻይናው አቻቸው ማ ዚንሚን በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይዋን በራሷ መንገድ ያለማንም ጣልቃ ገብነት መፍታት መብቷ እንደሆነ ገልጸዋል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይን እና የኢትዮጵያ-ሱዳን ድንበርን በተመለከተ በድርድር እና ሠላማዊ መንገድ ሊፈታ እንደሚገባ የሀገራቸው አቋም እንደሆነ ተናግረዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

አያይዘውም ሀገራቸው የአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የሶስትዮሽ ድርድር እንደምትደግፍ አስታውቀዋል።