መስከረም 7/2015 (ዋልታ) አሸባሪው ህወሓት “ሰላም” የሚለው ጊዜ ገዝቶ ጦርነቱን የማራዘም ፍላጎት ስላለው ነው ሲሉ በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ ገለጹ።
የሽብር ቡድኑ ከዚህ ቀደም መንግስት ያወጃቸውን የተኩስ አቁሞችና ያቀረበውን የሰላም ጥሪ “ጦርነቱን አሸንፊያለሁ” በሚል ማጣጣሉንና ውድቅ ማድረጉን አምባሳደር ፍጹም በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ ገልጸዋል።
ቡድኑ በለመደው የስርቆት ተግባሩ በመቀጠል ለሰብአዊ እርዳታ የሚውል ከ500 ሺሕ ሊትር በላይ ነዳጅ መዝረፉን አመልክተዋል።
አሸባሪው ቡድን በአፍራሽ ተግባሩ ቢቀጥልም የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላም የዘረጋውን እጅ አላጠፈም ብለዋል።
“የሽብር ቡድኑ ከሰሞኑ ሰላም እፈልጋለሁ በሚል ያወጣው መግለጫ ጊዜ መግዣና ራሱን ለጦርነት የማዘጋጃ አካሄድ ነው” ሲሉም አክለዋል።
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!