አሸባሪው ህወሓት እንስሳትን በመግደልና በመዝረፍ የህዝብ ጠላት መሆኑን እያሳየ ነው

አሸባሪው ህወሓት እንስሳትን መግደል

ጳጉሜ 2/2014 (ዋልታ) አሸባሪው ህወሓት በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጋዝጊብላ ወረዳ ዛሮታ ቀበሌ የአርሶ አደር ንብረት እንስሳቶችን በመግደልና በመዝረፍ ዋነኛ የህዝብ ጠላት መሆኑን አሳየ።

በወራሪው ቡድን ጉዳት የደረሰባቸው አርሶ አደሮች “አርሰን፣ አምርተን ልጅ እናሳድግበታለን፤ ከእርሻ በተጨማሪ ህይወታችን እንመራበታለን፤ እንገለገልባቸዋለን ብለን የምንተማመንባቸውን በሬ፣ ፍየልና በግ እንዲሁም ዶሮ በአሸባሪ ቡድኑ ተገድለውብናል” ብለዋል።

የቻለውን በልቶ እንስሳቱን በግፍ በመግደል ከጥቅም ውጭ ማድረጉም ተገልጿል።

እንስሳት በመዝረፍና መግደል ቡድኑ ለአርሶ አደሩ ያለውን ከፍተኛ ጥላቻ ያሳየበት ሰይጣናዊ ድርጊት እንደሆነም ተጓጂዎች አስረድተዋል።

የወራሪው ህወሓት ዋነኛ ዓላማው አርሶ አደሩ እንዳያርስና እንዳያመርት በማድረግ ህዝቡን ለችግር፣ ርሀብ፣ ስቃይና መከራ መዳረግና አጠቃላይ ኢኮኖሚውን መጉዳት መሆኑንም ተናግረዋል።

ወራሪው ቡድን ‘‘ከህዝብ ጋር ፀብ የለኝም፣ ጠላቴ የአማራ አመራር ነው’’ እያለ በአፈ ቀላጤዎቹና ሚዲያዎቹ የሚለፍፈው ፍፁም ሀሰት መሆኑን በጭካኔ ተግባሩ ማስመስከሩም ነው የተገለጸው።

አሸባሪው በክፋት ተወልዶ በክፋት ያደገ በክፋቱም ወደ መቃብር እየወረደ ያለ ዓላማ ቢስ ቡድን እንደሆነ አውቆ የሚሰጠውን የውሸትና የመከፋፈያ ሃሳብ ወደ ጎን ብሎ በአንድነትና በቁርጠኝነት መታገል ያስፈልጋል በማለት ተጓጂዎቹ ማሳሰባቸውን ከዞኑ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW