ከዓባይ ተፋስስ ሀገራት የተውጣጡ አባላት ያሉት ልዑክ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጎበኘ

ጳጉሜ 2/2014 (ዋልታ) ከተለያዩ የዓባይ ተፋስስ ሀገራት የተውጣጡ አባላት ያሉት ልዑክ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክትን ጎበኘ።

ልዑኩ በምርምር ተቋማት የሚሰሩ የውሃ ሃብት ምሁራን፣ በየአገራቱ የቀድሞ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የሚዲያ ባለሙያዎችን ያካተተ ነው ተብሏል።

የልዑካን ቡድኑ አባላት ከትናንት በስቲያ በአዲስ አበባ በተጀመረው የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት ምክንያታዊና ፍትሐዊ የውሃ ሃብት አጠቃቅም ላይ የሚመክረው ቀጣና አቀፍ የዓባይ ጉባዔ ላይ ለመታደም የመጡ ናቸው።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የኢትዮጵያ ምሁራንም በጉብኝቱ መሳተፋቸውን የኢዜአ ዘገባ አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW