አሸባሪው ሕወሓት ያወደማቸውን የጤና ተቋማት ጉብኝት

መስከረም 15/2014 (ዋልታ) የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በሰሜን ጎንደር ዞን ዛሪማ ከተማ አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በጤና ተቋማት ላይ ያደረሰውን ውድመት ተመልክተዋል፡፡

አሸባሪ ቡድኑ በዛሪማ ከተማ የሚገኘውን ጤና ጣቢያ በማውደም ከጥቅም ውጪ አድርጎታል።

መድኃኒቶች እና ልዩ ልዩ የህክምና መሳሪያዎችም በአሸባሪ ቡድኑ ተዘርፈዋል ሲል ኢብኮ ዘግቧል።

አሸባሪ ቡድኑ ከተማዋን ለሳምንታት ተቆጣጥሮ በነበረበት ወቅት ከጤና ተቋማት በተጨማሪ ትምህርት ቤቶችንና የመንግሥት ተቋማትን ያወደመ ሲሆን ባንክም መዝረፉን መዘገባችን ይታወሳል።