አሸባሪ ሕወሓትን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ ተካሄደ

አሸባሪ ሕወሓትን የሚያወግዝ ሰልፍ

መስከረም 9/2015 (ዋልታ) አሸባሪው ሕወሓት የከፈተውን ጦርነት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ ተካሄደ።

ዋይት ሐውስ ፊት ለፊት በተከናወነው ሰልፍ ኢትዮጰያውያን፣ ኤርትራውያን፣ ሶማሊያውያንና ሌሎች የኢትዮጵያ ወዳጆች መሳተፋቸው ተገልጿል።

ሰላማዊ ሰልፈኞቹ አሸባሪው ሕወሓት በኢትዮጵያ ላይ የከፈተውን ዳግም ወረራ የሚያወግዙና “አሜሪካ የሽብር ቡድኑ እየፈጸመ ያለውን አፍራሽ ድርጊት በማውገዝ ተጠያቂ ማድረግ አለባት፣ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን መቆም ይኖርባታል” የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።

የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ፣ በኤርትራና በአጠቃላይ በአፍሪካ ቀንድ የምትከተለውን የተሳሳተ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዳግም ልታጤነው እንደሚገባም የሚያሳስቡ መልዕክቶች መተላለፋቸውን ከሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ማህበር ዲሲ ግብረ ኃይል ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።

ሰላማዊ ሰልፉን ሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ማህበር ዲሲ ግብረ ኃይል በአሜሪካ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ አባላት፣ ከተለያዩ ተቋማትና አገር ወዳጆች ጋር በመተባበር እንዳዘጋጀውም ተገልጿል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW